Kambolojo
Welcome
Login / Register
data-ad-client="ca-pub-4109185011805854" data-ad-slot="8420426729" data-ad-format="auto">

Saturday News on Kambolojo

የእለተ ቅዳሜ ምሳ ሰዓት እግር ኳሳዊ ዜናዎች 

★የቬንገር ቆይታ በኤምሬትስ ...... ★
✔ከሁለት አስርት አመታት በላይ በመድፈኞቹ ቤት በመቆየት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን የአጨዋወት ዘይቤ የቀየሩት የመድፈኞቹ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በመጪው ክረምት ኮንትራታቸው እንደሚጠናቀቅ ይታወቃል፡፡እናም የመልካም እግር ኳስ አቀንቃኙ ሰው በኤምሬትስ ከዚህ በኃላ ስለሚኖራቸው ቆይታ ተጠይቀው ቆይታቸውን የሚወስኑት በአመቱ መጨረሻ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡አርሰን ቬንገር በ20 አመት ቆይታቸው ለመድፈኞቹ 9 ዋንጫዎችን ያሳኩ ሲሆን ፕሪሚየር ሊጉን ከ2004 በኃላ ወደ ሰሜን ለንደኑ ክለብ እንዳላመጡ ይታወቃል ፡፡★ሮናልዶ ቤልን እና ክሩስን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰን ነበር★
✔ታላቁን አሰልጣኝ ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በመተካት በ2013 ወደ ማን ዩናይትድ በአሰልጣኝነት ተሹመው መምጣታቸውን እናስታውሳለን ዴቪድ ሞይስ፡፡በኦልድትራፎርድ ከ10 ወራት በኃላ የተሰናበቱት ስኮቲሹ አሰልጣኝ ሮናልዶን ቤልን እና ቶኒ ክሮስን ለማስፈረም ጥረት አድርገው እንዳልተሳካላቸው ተናግረዋል ፡፡

"ቶኒ ክሮስ ያኔ በክረምቱ ለመምጣት ተስማምቶ ነበር ፤የሚገርመው ከራሱ ጋር እንዲሁም ከወኪሉ ጋር ጭምር ቃል በቃል ተነጋግረን ተማምነን ነበር እንደሚመጣ.......ሌላኛው ደግሞ ቤል ነው እኔ ወደ ዩናይትድ ስመጣ የመጀመሪያው እቅዴ ቤልን ማምጣት ነበር፤ቤል የዩናይትድ እንዲሆን የተቻለኝን ጥረት አርጌለው እስከ መጨረሻው ደቂቃ ጥሪያለው ለዩናይትድ የሚገባ ተጨዋች ነበር፤በቃ እሱ ግን መሄድ የፈለገው ወደ ሪያል ማድሪድ ነው" የወቅቱ የሰንደርላንድ አሰልጣኝ ስለ ሮናልዶም ተናግረዋል

"ትዝ ይለኛል ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈርጉሰን ጋር ስንገናኝ ሮናልዶ ወደ ዩናይትድ የመመለስ እድል እንዳለው ነገሩኝ እኛመም ሞከርን ግን አልተሳካም " ብለዋል፡፡★ያሁኑ ቼልሲ ከማይበገረው አርሰናል ጋር አይነፃፀርም★
✔የቀድሞው የመድፈኞቹ አማካይ ፖል ሜርሰን የኮንቴው ቼልሲ ከማይበገሩት (2003/2004) የአርሰናል ተጨዋቾች ጋር እንደማይነፃፀሩ ተናገረ፡፡

"ያኔ የነበረው የአርሰናል የምንጊዜም ምረጥ ትውልድ ሙለሉ አመቱን አንዴም አልተሸነፈም የሚገርም ነበር የቼልሲን ወቅታዊ አቋም ስናይ ጥሩ ነው ግን ግን ከያኔው የአርሰናል የምንጊዜም ምርጥ ቡድን በጥራት ያነሰ ነው" ነው፡፡★ማን ዩናይትድ ለዝላታን የአሰልጣኝነት ድርሻ ሊሰጠው ነው★
✔ እንደ እንግሊዙ ጋዜጣdaily star ዘገባ ከሆነ ማን ዩናይትድ ለግዙፉ የ35 አመት ስዊድናዊው ኢንተርናሽናል ኢብራሂሞቪች የአሰልጣኝነት ድርሻ ሊሰጠው አስቧል ፤ስዊድናዊው ጥበበኛ ወደ ሩቅ ምስራቅ ከመሄድ ይልቅ የጆዜ ሞሪንሆ ምክትል ሆኖ መስራት እንደሚፈልግም ተነግሯል ፤ዝላታን በዚህ አመት ለዩናይትድ 11 የፕሪሚየር ሊግ ግቦችን አስቆጥሯል የሚገርመው በዩናይትድ የሱን ግማሽ ራሱ ያስቆጠረ ሰው አለመኖሩ ነው፡፡★ እግር ኳስን እንደ ክሪስማስ ስጦታ አያታለው ★
✔ ከአሮጊቷ ጁቬንቱስ ወደ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በመምጣት የሚገርም ጠንካራ ቲም የሰራው ኮንቴ ለክሪስማስ ምንም አይነት እቃ መግዛት እንደማይፈልግ እና እግር ኳስን እንደ ክሪስማስ ስጦታ እንደሚያያት ለጋዜጠኞች ተናግሯል ፡፡በዓሉን ከቤተሰቦቹ ጋር እንደሚያሳልፍ እና እንግሊዝ ጥሩ የህይወት ልምድ እየሰጠችው እንደሆነ ተናግሯል ፡፡★ ለብር የሚጫወት ሰው ክለቤ ውስጥ እንዲኖር አልፈልግም ★
✔ ጀርመናዊው የገጌም pressing አቀንቃኝ ጀርደን ክሎፕ ከሰሞኑ በጣም ወጣት ተጨዋቾች ለገንዘብ ወደ ቻይና እና በጣም የሚፈልጉት ተጨዋች ድራክስለር ወደ ፔዤ ለመሄድ መስማማቱን ተከትሎ ሀሳባቸውን በብስጭት ገልፀዋል ፡፡

" ተጨዋቾች ማወቅ ያለባቸው መስራት ያለባቸው ለገንዘብ አይደለም መታመን ያለባቸው ለገንዘብ አይደለም መታመን ያለባቸው ለሙያቸው እና ለስራቸው ነው" በማለት በምሬት ተናግረዋል፡፡★ክሪስታል ፓላስ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ★
✔ ከሁለት ቀናት በፊት አሰልጣኙን አሰናብቶ የነበረው ክሪስታል ፓላስ ሳም አላርዳይስን ሾሟል፡፡★ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሶርያ ለሚገኙ ህፃናት መልዕክት አስተላለፈ★
✔ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በሲሪያ በጦርነት ለተጎዱ ህፃናት
መልዕክቱን አስተላልፏል። የሪያል ማድሪዱ ኮከብ
በትዊተር ፕሮፋይሉ የሚከተለውን ተስፋ ሰጪ መልዕክት
የያዘ ቪዲዮ ለቇል።
.
"ሄሎ! ይህ ለሲሪያ ህፃናት ነው። ብዙ እንደተጎዳቹ
እናውቃለን፣ እኔ ታዋቂ ተጫዋች ነኝ፣ እናንተ ግን
እውነተኛ ጀግኖች ናቹ። ተስፋችሁን አትጡ፣ አለም
ከእናንተ ጋር ነው፣ ለእናንተ እንጨነቃለን፣ እኔም
ከእናንተ ጋር ነኝ" ብሏል።

Post your comment

Sign in or sign up to post comments.

Comments

Be the first to comment
RSS